የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስድ​ስት ቀን ቂጣ እን​ጀራ ብላ፤ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን መው​ጫው ስለ​ሆነ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ይሁን፤ ለነ​ፍ​ስም ከሚ​ሠ​ራው በቀር ሥራን ሁሉ አታ​ድ​ር​ግ​በት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለስድስት ቀን እርሾ የሌለበት ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ጉባኤ አድርግ፤ ሥራም አትሥራበት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስድስት ቀን ያልቦካ ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለጌታ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሚከተሉት ስድስት ቀኖች ደግሞ እርሾ ሳይነካው የተዘጋጀ ቂጣ ትበላለህ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትሰግድ ዘንድ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስድስት ቀን ቂጣ እንጀራ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ጉባኤ ይሁን፤ ሥራን ሁሉ አታድርግበት።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 16:8
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ቀድሶ፥ ሰባት ቀን በዓል አድ​ርጎ ነበ​ርና በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የፍ​ጻሜ በዓል አደ​ረገ።


ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨ​ረ​ሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ መጽ​ሐፍ ያነ​ብብ ነበር። በዓ​ሉ​ንም ሰባት ቀን ያህል አደ​ረጉ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን እንደ ሕጋ​ቸው ወጡ።


ጾምን ቀድሱ፤ ምህ​ላ​ንም ዐውጁ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንና በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሰብ​ስቡ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ጩኹ።


ሰባት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ፤ ስም​ን​ተ​ኛ​ዋም ቀን የተ​ቀ​ደ​ሰች ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ፤ የመ​ሰ​ና​በቻ በዓል ነውና፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።


ሰባ​ተ​ኛ​ውም ቀን የተ​ቀ​ደሰ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።