ያን ጊዜም እነዚያ ሰዎች ወደ ንጉሡ ተሰብስበው ንጉሡን፥ “ንጉሥ ሆይ! ንጉሡ ያጸናው ትእዛዝ ወይም ሥርዐት ይለወጥ ዘንድ እንዳይገባ የሜዶንና የፋርስ ሕግ እንደ ሆነ ዕወቅ” አሉት።