ንጉሡም አስማተኞቹንና ከለዳውያኑን፥ ቃላተኞቹንም ያገቡ ዘንድ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ንጉሡም የባቢሎንን ጠቢባን፥ “ይህን ጽሕፈት ያነበበ፥ ፍቺውንም የነገረኝ ሐምራዊ ግምጃ ይለብሳል፤ የወርቅም ማርዳ በአንገቱ አስርለታለሁ፤ በመንግሥቴም ላይ ሦስተኛ ገዥ አድርጌ እሾመዋለሁ” ብሎ ተናገረ።