በሰማይ አምላክ በእግዚአብሔር ላይ ኰራህ፤ የመቅደሱንም ዕቃዎች በፊትህ አመጡ፤ አንተም መኳንንትህም፥ ሚስቶችህም፥ ቁባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው፤ ከብርና ከወርቅም፥ ከናስና ከብረትም፥ ከእንጨትና ከድንጋይም የተሠሩትን፥ የማያዩትንና የማይሰሙትንም፥ የማያውቁትንም አማልክት አመሰገንህ፤ ትንፋሽህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ ግን አላመሰገንኸውም።