ልዑል አምላክም የሰዎችን መንግሥት እንዲገዛ፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስኪያውቅ ደረስ ከሰው ልጆች ተለይቶ ተሰደደ፥ ልቡም እንደ አውሬ ልብ ሆነ፤ መኖሪያውም ከምድረ በዳ አህዮች ጋር ነበረ፤ እንደ በሬም ሣር በላ፤ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ።