ብልጣሶርም የወይን ጠጅ በጠጣ ጊዜ ንጉሡና መኳንንቱ፥ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ይጠጡባቸው ዘንድ፥ “አባቴ ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ያመጣቸውን የወርቁንና የብሩን ዕቃዎች አምጡ” ብሎ አዘዘ።