አሁንም ይህን ጽሕፈት ያነብቡ ዘንድ፥ ፍቺውንም ይነግሩኝ ዘንድ ጠንቋዮችና ፈላስፎች፥ ጠቢባንና ሟርተኞችም ወደ እኔ ገብተው ነበር፤ ነገር ግን የነገሩን ፍቺ ይነግሩኝ ዘንድ አልቻሉም።