የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያለበት ሰው በመንግሥትህ ውስጥ አለ፤ በአባትህም ዘመን እንደ አማልክት ጥበብ ያለ ጥበብና ማስተዋል፥ ዕውቀትም ተገኘበት፤ አባትህ ንጉሡ ናቡከደነፆር የሕልም ተርጓሚዎችና የአስማተኞች፥ የከለዳውያንና የቃላተኞች አለቃ አድርጎ ሾመው።