ያን ጊዜም ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል አንድ ሰዓት ያህል ዐሰበ፤ ልቡም ታወከ። ንጉሡም መልሶ፥ “ብልጣሶር ሆይ! ሕልሙና ፍቺው አያስቸግርህ” አለው። ብልጣሶርም መልሶ አለ፥ “ጌታዬ ሆይ! ሕልሙ ለሚጠሉህ፥ ፍቺውም ለጠላቶችህ ይሁን።