ቅጠሎቹም የተዋቡ ነበሩ፤ ፍሬውም ብዙ ነበረ፤ ሁሉም ከእርሱ ይመገብ ነበረ፤ ከጥላውም በታች የዱር አራዊት ያርፉበት ነበር፥ በቅርንጫፎቹም ውስጥ የሰማይ ወፎች ይቀመጡ ነበር፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ ከእርሱ ይበላ ነበር።