አለቆች፥ መሳፍንቱና ሹሞቹም፥ አዛዦቹና የንጉሡ ኃያላን ተሰብስበው እሳቱ ሰውነታቸውን እንዳልበላው፥ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተነካ፥ ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፥ የእሳቱም ሽታ በላያቸው እንዳልነበረ አዩ።