ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹሞችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፥ መጋቢዎችንም፥ አውራጃ ገዢዎችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፥ ንጉሡ ናቡከደነፆርም ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ።