የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ፥ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፤ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፤ እርሱም ተናገረ፤ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ።