ከለዳውያኑም በንጉሡ ፊት መልሰው፥ “የንጉሡን ነገር ያሳይ ዘንድ የሚችል ሰው በምድር ላይ የለም፤ ታላቅ ንጉሥና አለቃ የሆነ እንደዚያ ያለ ነገር የሕልም ተርጓሚንና አስማተኛን፥ ከለዳዊንም የሚጠይቅ የለም።