እነርሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ፤ የተክሉንም ቦታ በር ዘግተው ያዘዘቻቸውን ያመጡ ዘንድ በስርጥ ጎዳና ወጡ፤ የተሰወሩ እነዚያን መምህራን ግን አላዩአቸውም ነበር።