ነውር የሌለባቸውንና መልከ መልካሞቹን፥ በጥበብ ሁሉ የሚያስተውሉትን፥ ዕውቀትም የሞላባቸውን፥ አስተዋዮች የሆኑትን፥ በንጉሡም ቤት መቆም የሚችሉትን ብላቴኖች ያመጣና የከለዳውያንንም ትምህርትና ቋንቋ ያስተምሩአቸው ዘንድ ነገረው።