እግዚአብሔርም የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምን፥ ከእግዚአብሔርም ቤት ዕቃ ከፍሎ በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ወደ ሰናዖር ምድር ወደ ጣዖቱ ቤት ወሰደው፥ ዕቃውንም ወደ ጣዖቱ ግምጃ ቤት አገባው።