ቈላስይስ 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅግ እንደሚወዳችሁና ስለ እናንተ በሎዶቅያና በኢያራ ከተማ ስላሉትም እንደሚቈረቈር እኔ ምስክሩ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ስለ እናንተ እንዲሁም በሎዶቅያና በኢያራ ከተሞች ስላሉት ተግቶ እንደሚሠራ እኔ እመሰክርለታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እናንተ በሎዶቅያም በኢያራ ከተማም ስላሉቱ እጅግ በሥራ እንደደከመ እመሰክርለታለሁና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ እናንተ በሎዶቅያና በሂራፖሊስ ከተሞች ስላሉትም ሰዎች በጣም እንደሚደክም እኔ ራሴ እመሰክርለታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ እናንተ በሎዶቅያም በኢያራ ከተማም ስላሉቱ እጅግ እንዲቀና እመሰክርለታለሁና። |
እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።