የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




አሞጽ 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ከም​ሥ​ራቅ አን​በጣ ይመ​ጣል፤ አን​ዱም ኵብ​ኵባ ንጉሡ ጎግ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጌታ እግዚአብሔር ይህን አሳየኝ፤ የንጉሡ የመኸር እህል ከተሰበሰበ በኋላ ገቦው መብቀል በጀመረ ጊዜ፣ እርሱ የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ መከር ካለፈ በኋላ ያለው እህል በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፤ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ ማንም ሰው ሳይዘራው የበቀለ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጌታ እግዚአብሔር ይህን ራእይ አሳየኝ፤ እነሆ የንጉሡ የመከር እህል ከታጨደ በኋላ እንደገና ገቦ ሆኖ በበቀለው እህል ላይ እግዚአብሔር የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፥ እነሆም፥ የኋለኛው ሣር በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፥ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ የበቀለ የገቦ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት



አሞጽ 7:1
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አን​በጣ እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ሰብ ትን​ሹም ትል​ቁም ምር​ኮ​አ​ችሁ እን​ዲሁ ይሰ​በ​ሰ​ብ​ላ​ች​ኋል።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ ኢኮ​ን​ያ​ንን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች፥ ብል​ሃ​ተ​ኞ​ች​ንና እስ​ረ​ኞ​ችን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ማርኮ ወደ ባቢ​ሎን ከአ​ፈ​ለ​ሳ​ቸው በኋላ፥ እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ፊት የተ​ቀ​መጡ ሁለት የበ​ለስ ቅር​ጫ​ቶ​ችን አሳ​የኝ።


ያየ​ሁ​ትም ራእይ ከእኔ ወጣ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያሳ​የ​ኝን ነገር ሁሉ ለም​ር​ኮ​ኞች ተና​ገ​ርሁ።


ከተ​ምች የቀ​ረ​ውን አን​በጣ በላው፤ ከአ​ን​በ​ጣም የቀ​ረ​ውን ደጎ​ብያ በላው፤ ከደ​ጎ​ብ​ያም የቀ​ረ​ውን ኩብ​ኩባ በላው።


የሰ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ ታላቁ ሠራ​ዊቴ አን​በ​ጣና ደጎ​ብያ፥ ኩብ​ኩ​ባና ተምች ስለ በላ​ቸው ዓመ​ታት እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


በአ​ባ​ርና በቸ​ነ​ፈር መታ​ኋ​ችሁ፤ አት​ክ​ል​ታ​ችሁ፥ ወይ​ና​ች​ሁና በለ​ሳ​ችሁ፥ ወይ​ራ​ች​ሁም ከበጀ በኋላ ተምች በላው፤ ይህም ሆኖ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ፍ​ረድ በቃሉ እሳ​ትን ጠራ፤ እር​ስ​ዋም ታላ​ቁን ቀላ​ይና ምድ​ርን በላች።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም አንድ ሰው በቱ​ንቢ በተ​ሠራ ቅጥር ላይ ቆሞ ነበር፤ በእ​ጁም ቱንቢ ነበር።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም የቃ​ር​ሚያ ፍሬ የሞ​ላ​በት ዕን​ቅብ ነበረ።


እግዚአብሔርም አራት ጠራቢዎች አሳየኝ።


ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፣ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።