የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሐዋርያት ሥራ 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምን​አ​ል​ባት በመ​ን​ገድ የሚ​ያ​ገ​ኘው ሰው ቢኖር ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እያ​ሰረ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ላሉት ምኵ​ራ​ቦች የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ ከሊቀ ካህ​ናቱ ለመነ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የጌታን መንገድ የሚከተሉትን ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን በዚያ ካገኘ አስሮ ወደ ኢየሩሳሌም ለመውሰድ እንዲችል፣ በደማስቆ ለነበሩት ምኵራቦች ደብዳቤ እንዲሰጠው ሊቀ ካህናቱን ለመነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የጌታንም መንገድ የሚከተሉትን ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ሲያገኝ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት የሚያስችል ደብዳቤ ለደማስቆ ምኵራቦች ተጽፎ እንዲሰጠው ሊቀ ካህናቱን ጠየቀ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሐዋርያት ሥራ 9:2
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ ጋር በሌ​ሊት ደረ​ሰ​ባ​ቸው፤ መታ​ቸ​ውም፤ በደ​ማ​ስቆ ግራ እስ​ካ​ለ​ች​ውም እስከ ሖባ ድረስ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።


ስለ ደማ​ስቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። “እነሆ፥ ደማ​ስቆ ከከ​ተ​ሞች መካ​ከል ተለ​ይታ ትጠ​ፋ​ለች፤ ትፈ​ር​ሳ​ለ​ችም።


“ስለ ደማ​ስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰም​ተ​ዋ​ልና ሐማ​ትና አር​ፋድ አፈሩ፤ ቀለ​ጡም፤ እንደ ባሕ​ርም ተነ​ዋ​ወጡ፤ ያር​ፉም ዘንድ አይ​ች​ሉም።


ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም።


እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ የተ​ማረ ነበር፤ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሊያ​ስ​ተ​ም​ርና ሊመ​ሰ​ክር ከልቡ የሚ​ተጋ ነበር፤ ነገር ግን የዮ​ሐ​ን​ስን ጥም​ቀት ብቻ ተጠ​ምቆ ነበር።


በዚ​ያም ወራት ስለ​ዚህ ትም​ህ​ርት ብዙ ሁከት ሆነ።


በተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ውም ሕዝብ ፊት አን​ዳ​ን​ዶች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትም​ህ​ርት ላይ ክፉ እየ​ተ​ና​ገሩ ባላ​መኑ ጊዜ፥ ጳው​ሎስ ከእ​ነ​ርሱ ተለየ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም ይዞ ጢራ​ኖስ በሚ​ባል መም​ህር ቤት ሁል​ጊዜ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር።


ነገር ግን ይህን አረ​ጋ​ግ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ እኔ በሕግ ያለ​ውን፥ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ አምኜ እነ​ርሱ ክህ​ደት ብለው በሚ​ጠ​ሩት ትም​ህ​ርት የአ​ባ​ቶ​ችን አም​ላክ አመ​ል​ከ​ዋ​ለሁ።


ፊል​ክስ ግን አይ​ሁድ ከጥ​ንት ጀምሮ የክ​ር​ስ​ቲ​ያ​ንን ወገ​ኖች ሕግና ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ቃ​ወሙ ያውቅ ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም “እን​ኪ​ያስ የሺ አለ​ቃው ሉስ​ዮስ በመጣ ጊዜ ነገ​ራ​ች​ሁን እና​ውቅ ዘንድ እን​መ​ረ​ም​ራ​ለን” ብሎ ቀጠ​ራ​ቸው።


ይህ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ረ​ግ​ሁት፤ ከሊ​ቃነ ካህ​ና​ትም ሥል​ጣን ተቀ​ብዬ ከቅ​ዱ​ሳን ብዙ​ዎ​ችን ወደ ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ሲገ​ድ​ሏ​ቸ​ውም አብሬ እመ​ክር ነበ​ርሁ።


“ይህ​ንም ለመ​ፈ​ጸም ከሊ​ቃነ ካህ​ናት ሥል​ጣን ተቀ​ብዬ ወደ ደማ​ስቆ ከተማ ሄድሁ።


የነጻ ወጭ​ዎች ከም​ት​ባ​ለው ምኵ​ራ​ብም ከቀ​ሬ​ናና ከእ​ስ​ክ​ን​ድ​ርያ፥ ከቂ​ል​ቅ​ያና ከእ​ስያ የሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን ይከ​ራ​ከ​ሩት ነበር።


እር​ሱም ወገ​ኖ​ቻ​ች​ንን ተተ​ን​ኵሎ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው፤ ወንድ ልጅ​ንም ሁሉ እን​ዲ​ገ​ድሉ አዘዘ።


ወደ​ዚ​ህም ከካ​ህ​ናቱ አለቃ አስ​ፈ​ቅዶ የመጣ ስም​ህን የሚ​ጠ​ሩ​ትን ሁሉ ሊያ​ስር ነው።”


የሰ​ሙ​ትም ሁሉ አደ​ነቁ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይህን ስም የሚ​ጠ​ሩ​ትን ሁሉ ይጠ​ላ​ቸው የነ​በ​ረው ይህ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ዚህ ወደ​ዚህ የመ​ጣው እያ​ሰረ ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?”


በደ​ማ​ስቆ ከተማ ከን​ጉሥ አር​ስ​ጣ​ስ​ዮስ በታች የሆነ የአ​ሕ​ዛብ አለቃ ሊይ​ዘኝ ወድዶ የደ​ማ​ስ​ቆን ከተማ ያስ​ጠ​ብቅ ነበር።


ከእኔ በፊት ወደ ነበ​ሩት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ወ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን ወደ ዐረብ ሀገር ሄድሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ ደማ​ስቆ ተመ​ለ​ስሁ።