የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሐዋርያት ሥራ 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቃሉ​ንም ሰም​ተው ያመኑ ብዙ ሰዎች ናቸው፤ ያመ​ኑት ወን​ዶች ቍጥ​ርም አም​ስት ሺህ ያህል ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሁን እንጂ ቃሉን ከሰሙት መካከል ብዙዎቹ አመኑ፤ የወንዶቹም ቍጥር ወደ ዐምስት ሺሕ ከፍ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፥ የወንዶችም ቍጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ቃላቸውን ከሰሙት ሰዎች ብዙዎቹ አመኑ፤ የአመኑትም ሰዎች ቊጥር ወደ አምስት ሺህ ከፍ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፥ የወንዶችም ቍጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሐዋርያት ሥራ 4:4
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


ክብ​ርና ጽድቅ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ርቁ ሁሉ ያፍ​ራሉ።


ስለ​ዚ​ህም እርሱ ብዙ​ዎ​ችን ይወ​ር​ሳል፤ ከኀ​ያ​ላ​ንም ጋር ምር​ኮን ይከ​ፋ​ፈ​ላል፤ ነፍ​ሱን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር ተቈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎ​ችን ኀጢ​አት ተሸ​ከመ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ተሰጠ።


እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የስ​ንዴ ቅን​ጣት በም​ድር ላይ ካል​ወ​ደ​ቀ​ችና ካል​ሞ​ተች ብቻ​ዋን ትኖ​ራ​ለች፤ ከሞ​ተች ግን ብዙ ፍሬን ታፈ​ራ​ለች።


ቃሉ​ንም ተቀ​ብ​ለው ተጠ​መቁ፤ በዚ​ችም ዕለት ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ተጨ​መሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግኑ ነበር፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ዘንድ መወ​ደድ ነበ​ራ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ድ​ኑ​ትን ዕለት ዕለት በእ​ነ​ርሱ ላይ ይጨ​ምር ነበር።


ከእ​ነ​ር​ሱም እኩ​ሌ​ቶቹ የተ​ና​ገ​ረ​ውን አመኑ፤ እኩ​ሌ​ቶቹ ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም።