የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሐዋርያት ሥራ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝ​ቡን ስለ አስ​ተ​ማ​ሩና በኢ​የ​ሱ​ስም የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ስለ ሰበኩ በእ​ነ​ርሱ ተና​ደዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም ሐዋርያት ሕዝቡን በማስተማራቸውና በኢየሱስ ስለ ተገኘው ትንሣኤ ሙታን በመስበካቸው እጅግ ተቈጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕዝቡን ስለ አስተማሩና በኢየሱስ የሙታንን ትንሣኤ ስለ ሰበኩ እጅግም ተቆጥተው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሁለቱ ሐዋርያት የኢየሱስን ከሞት መነሣት ለሕዝቡ በማስተማራቸውና በዚህም የሙታን ትንሣኤ መኖሩን በማስረዳታቸው ተቈጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሕዝቡን ስለ አስተማሩና በኢየሱስ የሙታንን ትንሣኤ ስለ ሰበኩ ተቸግረው፥ ወደ እነርሱ ቀረቡ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ሐዋርያት ሥራ 4:2
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላ​ጥና አገ​ል​ጋዩ አሞ​ና​ዊው ጦብያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መል​ካ​ምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበ​ሳጩ።


አይ​ሁ​ድም የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ውን ብዙ ሕዝብ ባዩ ጊዜ ቀኑ​ባ​ቸው፤ እየ​ተ​ሳ​ደ​ቡም ጳው​ሎስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ተቃ​ወሙ።


የኤ​ፌ​ቆ​ሮ​ስን ትም​ህ​ርት ከተ​ማሩ ፈላ​ስ​ፋ​ዎች መካ​ከ​ልና ረዋ​ቅ​ያ​ው​ያን ከሚ​ባ​ሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላ​ስ​ፎ​ችም የተ​ከ​ራ​ከ​ሩት ነበሩ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ችም፥ “ይህ ለፍ​ላፊ ምን ሊና​ገር ይፈ​ል​ጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ስለ መነ​ሣ​ቱም ሰብ​ኮ​ላ​ቸ​ዋ​ልና የአ​ዲስ አም​ላክ ትም​ህ​ር​ትን ያስ​ተ​ም​ራል” አሉ።


በዚ​ያም ወራት ስለ​ዚህ ትም​ህ​ርት ብዙ ሁከት ሆነ።


በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆሜ ከአ​ስ​ተ​ማ​ር​ኋት አን​ዲት ትም​ህ​ርት በቀር ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር የለም። ‘ሙታን ይነ​ሣሉ’ በማ​ለ​ቴም ዛሬ በአ​ንተ ዘንድ በእኔ ይፈ​ረ​ድ​ብ​ኛል።”


ክር​ስ​ቶስ እን​ደ​ሚ​ሞት፥ ከሙ​ታን ተለ​ይ​ቶም አስ​ቀ​ድሞ እን​ደ​ሚ​ነሣ፥ ለሕ​ዝ​ብና ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ፥ ለመ​ላ​ውም ዓለም እን​ደ​ሚ​ያ​በራ።”


እን​ዴ​ትስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙታ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው በእ​ና​ንተ ዘንድ የማ​ይ​ታ​መን ሆኖ ይቈ​ጠ​ራል?


የሕ​ይ​ወ​ትን ባለ​ቤት ግን ገደ​ላ​ች​ሁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ ለዚ​ህም እኛ ምስ​ክ​ሮቹ ነን።


ሊቀ ካህ​ና​ቱና አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት የሰ​ዱ​ቃ​ው​ያን ወገ​ኖ​ችም ቀን​ተው በእ​ነ​ርሱ ላይ ተነሡ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው እርሱ አድ​ሮ​ባ​ችሁ ባለ መን​ፈሱ ለሟች ሰው​ነ​ታ​ችሁ ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ታል።


ነገር ግን ሰው ሁሉ በየ​ሥ​ር​ዐቱ ይነ​ሣል፤ በመ​ጀ​መ​ሪያ ከሙ​ታን የተ​ነሣ ክር​ስ​ቶስ ነው፤ ከዚያ በኋላ በክ​ር​ስ​ቶስ ያመኑ እርሱ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ ይነ​ሣሉ።