የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሐዋርያት ሥራ 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ሞት ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ እን​ዲ​ነሣ፥ እየ​ተ​ረ​ጐ​መና እየ​አ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፥ “ይህ እኔ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው” ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ክርስቶስ መከራን መቀበል እንዳለበትና ከሙታንም መነሣት እንደሚገባው እያስረዳ በማረጋገጥ፣ “ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሲተረጉምም ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ዘንድ እያስረዳ “ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው፤” ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መሲሕ መከራ መቀበልና ከሞት መነሣት እንደሚገባው ገልጦ እያስረዳ “ይህ እኔ የማበሥራችሁ ኢየሱስ መሲሕ ነው” ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሲተረጉምም ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ዘንድ እያስረዳ፦ ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



ሐዋርያት ሥራ 17:3
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲህ አሉ፥ “በመ​ን​ገድ ሲነ​ግ​ረን፥ መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም ሲተ​ረ​ጕ​ም​ልን ልባ​ችን ይቃ​ጠ​ል​ብን አል​ነ​በ​ረ​ምን?”


እር​ሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነ​ቢ​ያ​ትና በመ​ዝ​ሙ​ርም ስለ እኔ የተ​ነ​ገ​ረው ይፈ​ጸም ዘንድ እን​ዳ​ለው፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላ​ቸው።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ሞት በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እን​ዲ​ነሣ፥


ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ይነሣ ዘንድ እንደ አለው በመ​ጻ​ሕ​ፍት የተ​ጻ​ፈ​ውን ገና አላ​ወ​ቁም ነበ​ርና።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አብሮ ሳለ፥ “ከእኔ የሰ​ማ​ች​ሁ​ትን የአ​ብን ተስፋ ጠብቁ” ብሎ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዳ​ይ​ወጡ አዘ​ዛ​ቸው።


ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉም በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት አይ​ሁ​ድን በግ​ልጥ እጅግ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ ስለ ኢየ​ሱ​ስም እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ከመ​ጻ​ሕ​ፍት ማስ​ረጃ ያመ​ጣ​ላ​ቸው ነበር።


ሲላ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም ከመ​ቄ​ዶ​ንያ በወ​ረዱ ጊዜ ጳው​ሎስ፥ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ለአ​ይ​ሁድ እየ​መ​ሰ​ከረ ቃሉን በማ​ስ​ተ​ማር ይተጋ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ክር​ስ​ቶስ መከ​ራን እን​ዲ​ቀ​በል በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ አስ​ቀ​ድሞ እንደ ተና​ገረ እን​ዲሁ ፈጸመ።


ሳውል ግን እየ​በ​ረታ ሔደ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም ለነ​በ​ሩት አይ​ሁድ ይህ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ እያ​ስ​ረዳ መልስ አሳ​ጣ​ቸው።


እና​ንተ ሰነ​ፎች የገ​ላ​ትያ ሰዎች ሆይ፥ ለዐ​ይን በሚ​ታ​የው እው​ነት እን​ዳ​ታ​ምኑ ማን አታ​ለ​ላ​ችሁ? እር​ሱም እን​ዲ​ሰ​ቀል አስ​ቀ​ድሞ የተ​ጻ​ፈ​ለት ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው።