ስለ ወገኖችህ ስለ እስራኤልም እለምንሃለሁ፤ ስለ ተወደደው ስለ ሱራፌል ምስጋና፥ በጎ መዓዛ ስላለው ስለ ኪሩቤልም ዕጣን እለምንሃለሁ፤ የጽድቅ ሊቀ መላእክት ሚካኤልም በእውነት አመስጋኝ ነው፤ የሚያበራልኝ፥ ጻድቃንም እስከ ገቡባቸው ድረስ የጽድቅ በሮችን የሚከፍትልኝ እርሱ ነው።