ዳግመኛም እንደ ባሕር ሞገድ፥ ከምድርም አንሥቶ ትቢያን እንደሚበትን ጥቅል ነፋስ፥ ነፋስም እንደሚያናውጠው እንደ ባሕር ሞገድ የሚታወኩ ብዙ አሳቦች አሉት፤ እንደማይቈጠር እንደ ዝናብም ጠብታ በልቡ ከአለ ከማይቈጠር ከአሳቡ ብዛት የተነሣ የአዳም አሳብ እንደዚሁ ነው።