ስለዚህም እግዚአብሔር እንደ አንተ ከአሉ ከመላእክት አለቆች ሁሉ ለይቶ አዋረደህ፤ በአንድ ምክር የተፈጠራችሁ አንተና ሠራዊትህም ስለማይጠቅም ስለ ልቡናችሁ መደንደንና ስለ ሕሊናችሁ ትዕቢት ከእግዚአብሔር ምስጋና ወጥታችሁ ሳታችሁ፤ በሌላም ሳይሆን በፈጣሪያችሁ ላይ ታበያችሁ።