የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 20:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከዳ​ዊት ተለ​ይ​ተው የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡ​ሄን ተከ​ት​ለው ሄዱ፤ የይ​ሁዳ ሰዎች ግን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀም​ረው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስ​ኪ​ደ​ርሱ ንጉ​ሣ​ቸ​ውን ተከ​ተሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ የእስራኤል ሰው ሁሉ ዳዊትን ከድቶ የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ተከተለ። የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንሥቶ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ከንጉሣቸው ሳይለዩ ዐብረውት ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ የእስራኤል ሰው ሁሉ ዳዊትን ከድቶ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ተከተለ። የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንሥቶ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ከንጉሣቸው ሳይለዩ አብረውት ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም እስራኤላውያን ዳዊትን ከድተው ከሼባዕ ጋር ሄዱ፤ የይሁዳ ሕዝብ ግን ታማኝነታቸውን በማጽናት ከዮርዳኖስ እስከ ኢየሩሳሌም ዳዊትን ተከትለው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከዳዊት ተለይተው የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ተከተሉ፥ የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ ጀምረው ኢየሩሳሌም እስኪደርሱ ንጉሣቸውን ተከተሉ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 20:2
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም ተመ​ልሶ እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ መጣ። የይ​ሁዳ ሰዎ​ችም ንጉ​ሡን ሊቀ​በሉ፥ ንጉ​ሡ​ንም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሊያ​ሻ​ግሩ ወደ ጌል​ገላ መጡ።


በዚ​ያም አንድ ብን​ያ​ማዊ የቢ​ኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚ​ባል የዐ​መፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እር​ሱም፥ “ከዳ​ዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለ​ንም፦ ከእ​ሴ​ይም ልጅ ዘንድ ርስት የለ​ንም፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድህ ወደ ድን​ኳ​ንህ ተመ​ለስ” ብሎ መለ​ከት ነፋ።


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር የሚ​ሆን የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡሄ የሚ​ባል አንድ ሰው ግን በን​ጉሡ በዳ​ዊት ላይ እጁን አነሣ፤ እር​ሱን ብቻ​ውን ስጡኝ፤ እኔም ከከ​ተ​ማ​ዪቱ እር​ቃ​ለሁ” አላት። ሴቲ​ቱም ኢዮ​አ​ብን፥ “እነሆ፥ ራሱ ከቅ​ጥር ላይ ይጣ​ል​ል​ሃል” አለ​ችው።


ዳዊ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ቤቱ መጣ፤ ንጉ​ሡም ቤቱን ሊጠ​ብቁ የተ​ዋ​ቸ​ውን ዐሥ​ሩን ቁባ​ቶች ወስዶ ለጠ​ባቂ ሰጣ​ቸው፤ ቀለ​ብም ሰጣ​ቸው፤ ነገር ግን ወደ እነ​ርሱ አል​ገ​ባም፤ በቤ​ትም ተዘ​ግ​ተው እስ​ኪ​ሞቱ ድረስ መበ​ለ​ቶች ሆነው ተቀ​መጡ።


ከዚ​ህም በኋላ እስ​ራ​ኤል በሙሉ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከግ​ብፅ እንደ ተመ​ለሰ በሰሙ ጊዜ ልከው ወደ ሸን​ጎ​አ​ቸው ጠሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ አነ​ገ​ሡት። ከብ​ቻው ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ነገድ በቀር የዳ​ዊ​ትን ቤት የተ​ከ​ተለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


በይ​ሁዳ ከተ​ሞች የተ​ቀ​መ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ግን ሮብ​ዓ​ምን በላ​ያ​ቸው አነ​ገሡ።


እነ​ርሱ ግን ነፍ​ሴን ለከ​ንቱ ፈለ​ጓት፤ ወደ ምድር ጥልቅ ይግቡ።


የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።


በደ​ረሰ ጊዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸን​ተው ይኖሩ ዘንድ መከ​ራ​ቸው።