ነገር ግን ከእርሱ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ። አበኔርም በጦሩ ጫፍ ወገቡን ወጋው፤ ጦሩም በኋላው ወጣ፤ በዚያም ስፍራ ወድቆ በበታቹ ሞተ። አሣሄልም ወድቆ በሞተበት ስፍራ የሚያልፍ ሁሉ ይቆም ነበር።
2 ሳሙኤል 2:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብና አቢሳም አበኔርን አሳደዱ፤ ፀሐይም ጠለቀች፤ እነርሱም በገባዖን ምድረ በዳ መንገድ በጋይ ፊት ለፊት እስካለው እስከ አማን ኮረብታ ድረስ መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብና አቢሳ ግን አበኔርን ተከታተሉት፤ እያሳደዱም ወደ ገባዖን ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ከጋይ አጠገብ ወዳለው ወደ አማ ኰረብታ ሲደርሱ ፀሓይ ጠለቀች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብና አቢሳ ግን አበኔርን ተከታተሉት፤ ፀሐይ ስትጠልቅ ወደ ገባዖን ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ከጊያሕ አጠገብ ወዳለው ወደ አማ ኮረብታ ደርሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብና አቢሳ ግን አበኔርን አሳደዱት፤ ፀሐይ በጠለቀች ጊዜም ከጊያሕ በስተ ምሥራቅ፥ ወደ ገባዖን ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ወዳለው ወደ አማ ኮረብታ ደረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብና አቢሳም አበኔርን አሳደዱ፥ በገባዖንም ምድረ በዳ መንገድ በጋድ ፊት ለፊት እስካለው እስከ አማ ኮረብታ ድረስ በወጡ ጊዜ ፀሐይ ጠለቀች። |
ነገር ግን ከእርሱ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ። አበኔርም በጦሩ ጫፍ ወገቡን ወጋው፤ ጦሩም በኋላው ወጣ፤ በዚያም ስፍራ ወድቆ በበታቹ ሞተ። አሣሄልም ወድቆ በሞተበት ስፍራ የሚያልፍ ሁሉ ይቆም ነበር።