2 ሳሙኤል 18:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ግን “አንተ ከእኛ ከሁላችን ይልቅ እንደ ዐሥር ሽህ ሠራዊት ስለሆንህ ብንሸሽ ልባቸው አይከተለንምና፥ እኩሌታችንም ብንሞት ልባቸው አይከተለንምና አትውጣ፤ አሁንም መርዳትን ትረዳን ዘንድ በከተማ ብትኖርልን ይሻለናል” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ ግን፣ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፣ ሰዎቹ ከቁም ነገር አይቈጥሩንም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት ደንታቸው አይደለም፣ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺሕ ትበልጣለህ፤ ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎቹ ግን፥ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺህ ትበልጣለህ! ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “አንተ ከእኛ ጋር መሄድ የለብህም፤ ጥቂቶቻችን ወደ ኋላ ተመልሰን ብንሄድ ወይም ግማሾቻችን ብንገደል ጠላት ምንም አይገደውም፤ አንተ ግን ከእኛ ዐሥሩን ሺህ ትበልጣለህ፤ ስለዚህ አንተ እዚሁ በከተማይቱ ውስጥ ቈይተህ አስፈላጊውን ርዳታ ብትልክልን ይሻላል” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡ ግን፦ አትወጣም፥ ብንሸሽ ስለ እኛ አያስቡም፥ ከእኛም እኩሌታው ቢሞት ስለ እኛ አያስቡም፥ አንተ ግን ለብቻህ ከእኛ ከአሥሩ ሺህ ይልቅ ትበልጣለህ፥ አሁንም በከተማ ተቀምጠህ ብትረዳን ይሻላል አሉ። |
ደክሞና እጁ ዝሎ ሳለ እወድቅበታለሁ፤ አስፈራውማለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸሻል፤ ንጉሡንም ብቻውን እገድለዋለሁ፤
የሶርህያም ልጅ አቢሳ አዳነው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፥ “አንተ የእስራኤል መብራት እንዳትጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም” ብለው ማሉለት።
የሶርያም ንጉሥ ሠላሳ ሁለቱን የሰረገሎች አለቆች፥ “ከእስራኤል ንጉሥ በቀር፥ ታናሽ ቢሆን ወይም ታላቅ ከማናቸውም ጋር አትዋጉ” ብሎ አዝዞ ነበር።
ሬስ። ስለ እርሱ፥ “በአሕዛብ ውስጥ በጥላው በሕይወት እንኖራለን” ያልነው፥ በእግዚአብሔር የተቀባ፥ የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በወጥመዳቸው ተያዘ።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።