አቤሴሎምም፥ “ነገርና ክርክር ያለው ሁሉ ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ፥ ቅንም ፍርድ እፈርድለት ዘንድ በሀገር ላይ ፈራጅ አድርጎ ማን በሾመኝ?” ይል ነበር።
2 ሳሙኤል 15:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም፥ “ነገርህ መልካም ነው፤ ቀላልም ነው፤ ነገር ግን ከንጉሥ ዘንድ የሚሰማህ የለም” ይለው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አቤሴሎም፣ “ተመልከት! ጕዳይህማ ትክክልና ተገቢም ነው፤ የትኛው የንጉሥ እንደራሴ ነው ታዲያ የሚያይልህ?” ይለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አቤሴሎም፥ “ተመልከት! ጉዳይህማ ትክክልና ተገቢም ነው፤ ነገር ግን ከንጉሥ ተወክሎ የሚሰማህ የለም” ይለው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሴሎም፥ “ተመልከት፤ ሕግ አንተን ይደግፍሃል፤ ነገር ግን በንጉሡ ተወክሎ ጉዳይህን በትክክል የሚያይልህ የለም” ይለዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም፦ ነገርህ እውነትና ቅን ነው፥ ነገር ግን ከንጉሥ ታዝዞ የሚሰማህ የለም ይለው ነበር። |
አቤሴሎምም፥ “ነገርና ክርክር ያለው ሁሉ ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ፥ ቅንም ፍርድ እፈርድለት ዘንድ በሀገር ላይ ፈራጅ አድርጎ ማን በሾመኝ?” ይል ነበር።
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
“ከእስራኤል ልጆች አንዱን የሰረቀ ወይም ግፍ የፈጸመበት፥ ወይም አሳልፎ ቢሰጠው፥ ወይም በእርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ እርሱ ይገደል።
በአንቺ ውስጥ አባትንና እናትን አቃለሉ፤ በመካከልሽ በመጻተኛው ላይ በደልን አደረጉ፤ በአንቺ ውስጥ ድሀ አደጉንና መበለቲቱን አስጨነቁ።
በሙሴና በአሮን ላይ ተነሡ፤ “ለእናንተ ይበቃችኋል፤ ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ እግዚአብሔርም በመካከላቸው ነውና፤ በእግዚአብሔርስ ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ?” አሉአቸው።
ጳውሎስም፥ “ወንድሞች፥ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላውቅም መጽሐፍ ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ አትናገር’ ይላልና” አላቸው።