የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 14:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ሁም የቴ​ቁ​ሔ​ዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ወደ​ቀች፤ ሰግ​ዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አድ​ነኝ” አለች።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የቴቁሔዪቱም ሴት ወደ ንጉሡ ገብታ፣ በንጉሡ ፊት ወደ መሬት በግምባሯ ተደፍታ እጅ በመንሣት አክብሮቷን ከገለጠች በኋላ፣ “ንጉሥ ሆይ! እርዳኝ” አለች።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የተቆዓዪቱም ሴት ወደ ንጉሡ ገብታ፥ በንጉሡ ፊት በግምባሯ በምድር ላይ ተደፍታ እጅ በመንሣት፥ “ንጉሥ ሆይ! እርዳኝ” አለች።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሴቲቱም ወደ ንጉሡ ቀርባ ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ ነሣችና “ንጉሥ ሆይ! እባክህ እርዳኝ!” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲሁም የቴቁሔይቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግምባርዋ በምድር ላይ ወደቀች፥ እጅ ነሥታም፦ ንጉሥ ሆይ፥ አድነኝ አለች።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 14:4
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰ​ፈር ከሳ​ኦል ወገን አንድ ሰው ልብ​ሱን ቀድዶ፥ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊ​ትም በመጣ ጊዜ በም​ድር ላይ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።


ኢዮ​አ​ብም በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉ​ሡ​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገ​ስን እን​ዳ​ገኘ አገ​ል​ጋ​ይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።


ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት። እር​ስ​ዋም አለች፥ “በእ​ው​ነት እኔ ባሌ የሞ​ተ​ብኝ ባል​ቴት ሴት ነኝ።


አኪ​ማ​ሖ​ስም ጮኾ ንጉ​ሡን፥ “ሰላም ለአ​ንተ ይሁን!” አለው። በን​ጉ​ሡም ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ሰግዶ፥ “በን​ጉሡ በጌ​ታዬ ላይ እጃ​ቸ​ውን ያነ​ሡ​ትን ሰዎች አሳ​ልፎ የሰጠ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።


ብላ​ቴ​ና​ውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤ​ር​ገብ ተነሣ፤ በም​ድ​ርም ላይ በግ​ን​ባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእ​ር​ሳ​ቸ​ውም ተሳ​ሳሙ፤ ለረ​ዥም ሰዓ​ትም ተላ​ቀሱ።


አቤ​ግ​ያም ዳዊ​ትን ባየች ጊዜ ከአ​ህ​ያዋ ላይ ፈጥና ወረ​ደች፤ በዳ​ዊ​ትም ፊት በግ​ን​ባ​ርዋ ወደ​ቀች፤ ምድ​ርም ነክታ ሰገ​ደ​ች​ለት።