እርሻቸውን፥ የወይናቸውንና የወይራቸውን ቦታ፥ ቤታቸውንም፥ ከእነርሱም የወሰዳችሁትን ገንዘቡንና እህሉን፥ ወይን ጠጁንና ዘይቱን እባካችሁ ዛሬ መልሱላቸው።”
2 ሳሙኤል 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን አድርጎአልና፥ አላዘነምና ስለ አንዲቱ በግ አራት አድርጎ ይመልስ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ ያለውን ነገር በማድረጉና ባለማዘኑም ስለ በጊቱ አራት ዕጥፍ መክፈል አለበት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ ያለውን ነገር በማድረጉና ባለማዘኑም ስለ ግልገሊቱ አራት ዕጥፍ መክፈል አለበት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን የመሰለ የጭካኔ ሥራ በመፈጸሙ ከዚያ ሰው የወሰደበትን አራት እጥፍ አድርጎ መመለስ አለበት” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን አድርጎአልና፥ አላዘነምና ስለ አንዲቱ በግ አራት ይመልስ አለው። |
እርሻቸውን፥ የወይናቸውንና የወይራቸውን ቦታ፥ ቤታቸውንም፥ ከእነርሱም የወሰዳችሁትን ገንዘቡንና እህሉን፥ ወይን ጠጁንና ዘይቱን እባካችሁ ዛሬ መልሱላቸው።”
“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በአንድ በሬ ፋንታ አምስት በሬዎች፥ በአንድ በግም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል።
ወይም በሐሰት የማለበትን ነገር ቢመልስ፥ በሙሉ ይመልስ፤ ከዚያም በላይ አምስተኛውን ክፍል ጨምሮ የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን ለባለ ገንዘቡ ይስጠው።
ዘኬዎስም ቆመና ጌታችንን እንዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገንዘቤን እኩሌታ ለነዳያን እሰጣለሁ፤ የበደልሁትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከፍለዋለሁ።”