ኦርዮም ለዳዊት፥ “የእግዚአብሔር ታቦትና እስራኤል፥ ይሁዳም በድንኳን ተቀምጠዋል፤ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም አገልጋዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል፤ እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳለሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም” አለው።
2 ሳሙኤል 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም ኦርዮን፥ “አንተ ከመንገድ የመጣህ አይደለህምን? ስለምን ወደ ቤትህ አልወረድህም?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት፣ “ኦርዮን ወደ ቤቱ አልሄደም” መባሉን ሲሰማ ኦርዮን፣ “ከመንገድ ገና አሁን መግባትህ አይደለምን? ወደ ቤትህ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት፥ “ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” መባሉን ሲሰማ ኦርዮንን፥ “ከመንገድ ገና አሁን መግባትህ አይደለምን? ወደ ቤትህ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦርዮ ወደ ቤቱ አለመሄዱን ዳዊት በሰማ ጊዜ “ብዙ ጊዜ ከቤተሰብህ ተለይተህ እነሆ አሁን ገና መመለስህ ነው፤ ታዲያ ወደ ቤትህ ያልሄድከው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም ብለው ለዳዊት ነገሩት፥ ዳዊትም ኦርዮን፦ አንተ ከመንገድ የመጣህ አይደለምን? ስለ ምን ወደ ቤትህ አልወረድህም? አለው። |
ኦርዮም ለዳዊት፥ “የእግዚአብሔር ታቦትና እስራኤል፥ ይሁዳም በድንኳን ተቀምጠዋል፤ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም አገልጋዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል፤ እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳለሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም” አለው።
እግዚአብሔርም ነቢዩ ናታንን ወደ ዳዊት ላከ፤ ወደ እርሱም መጥቶ አለው፥ “በአንድ ከተማ አንዱ ባለጠጋ፥ አንዱም ድሃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ።