የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም፦ አንተ ማን ነህ? አለኝ፤ እኔም አማ​ሌ​ቃዊ ነኝ ብዬ መለ​ስ​ሁ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እርሱም፣ ‘አንተ ማን ነህ?’ ሲል ጠየቀኝ፤ “እኔም ‘አማሌቃዊ ነኝ’ ብዬ መለስሁለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም፥ ‘አንተ ማን ነህ?’ ብሎ ጠየቀኝ፤ እኔም ‘አማሌቃዊ ነኝ’ ብዬ መለስኩለት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ማን እንደ ሆንኩ በጠየቀኝ ጊዜም ዐማሌቃዊ መሆኔን ነገርኩት፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም፦ አንተ ማን ነህ? አለኝ፥ እኔም፦ አማሌቃዊ ነኝ ብዬ መለስሁለት።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 1:8
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ተመ​ል​ሰ​ውም ቃዴስ ወደ ተባ​ለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን አለ​ቆች ሁሉና በአ​ሳ​ሶን ታማር የሚ​ኖሩ አሞ​ራ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።


ዳዊ​ትም ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለ​ትን ጐል​ማሳ፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “እኔ የመ​ጻ​ተ​ኛው የአ​ማ​ሌ​ቃ​ዊው ልጅ ነኝ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ወደ ኋላ​ውም ዘወር አለና እኔን አይቶ ጠራኝ፤ እኔም፦ እነ​ሆኝ አልሁ።


እር​ሱም፦ ክፉ ጨለማ ይዞ​ኛ​ልና ደግሞ እስ​ካ​ሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያ​ውት ናትና በላዬ ቆመህ ግደ​ለኝ አለኝ።


ዐማ​ሌ​ቅ​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ዐማ​ሌቅ የአ​ሕ​ዝብ አለቃ ነበረ፤ ዘራ​ቸ​ውም ይጠ​ፋል።”


አሁ​ንም ሄደህ አማ​ሌ​ቅ​ንና ኢያ​ሬ​ምን ምታ፤ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፈጽ​መህ አጥፋ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ታ​ድ​ነው የለም። አጥ​ፋ​ቸው፤ መከ​ራም አጽ​ና​ባ​ቸው፤ የእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያ​ቸ​ውም፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ወን​ዱ​ንና ሴቱን፥ ብላ​ቴ​ና​ው​ንና ሕፃ​ኑን፥ በሬ​ው​ንና በጉን፥ ግመ​ሉ​ንና አህ​ያ​ውን ግደል።”


ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወጥ​ተው በጌ​ሴ​ራ​ው​ያ​ንና በአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ቅጽር ባላ​ቸው በጌ​ላ​ም​ሱ​ርና በአ​ኔ​ቆ​ን​ጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀ​ም​ጠው አገ​ኙ​አ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊ​ትና ሰዎቹ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ሴቄ​ላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን በአ​ዜብ በሰ​ቄ​ላ​ቅም ላይ ዘም​ተው ነበር፤ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም መት​ተው በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋት ነበር፥


ዳዊ​ትም፥ “አንተ የማን ነህ? ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ያም ግብ​ፃዊ ብላ​ቴና፥ “እኔ የአ​ማ​ሌ​ቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦ​ስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበ​ርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።


ዳዊ​ትም ሄዶ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ከሚ​ወ​ጣ​በት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግ​መ​ኛም በማ​ግ​ሥቱ መታ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በግ​መል ተቀ​ም​ጠው ከሸ​ሹት አራት መቶ ጐል​ማ​ሶች በቀር አን​ድም ያመ​ለጠ የለም።