2 ሳሙኤል 1:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሜ ዮናታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨነቃለሁ፤ አንተ በእኔ ዘንድ እጅግ የተወደድህ ነበርህ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ ዐዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ፤ ከሴት ፍቅርም ይልቅ ግሩም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ አዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ፤ ከሴት ፍቅርም ይልቅ የበረታ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወንድሜ ዮናታን ሆይ! እኔ ስለ አንተ በጣም አዘንኩ፤ አንተ ለእኔ በጣም ተወዳጅ ነበርክ። ፍቅርህ ለእኔ አስደናቂ ነበር፤ ይኸውም ከሴት ፍቅር የበረታ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሜ ዮናታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨነቃለሁ፥ በእኔ ዘንድ ውድህ እጅግ የተለየ ነበር፥ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ግሩም ነበረ። |
ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤርገብ ተነሣ፤ በምድርም ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእርሳቸውም ተሳሳሙ፤ ለረዥም ሰዓትም ተላቀሱ።