በመውጣትህና በመግባትህ፥ በሆድህም ፍሬ፥ በመንጋዎችህና በድልቦችህም፥ በጣቶችህም በአመለከትህበት ሥራ ሁሉ፥ በልብህም ባሰብኸው ሁሉ ደስ ይልሃል፤ እንዲህ ታደርግ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል፥ ታፈርስም ዘንድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሥልጣን ተሰጥቶሃልና ሁሉ ይታዘዝልሃል።