ኢያሱ አምስቱን የከነዓን ነገሥታትን በአንዲት ቀን በአንዲት ዋሻ እንደ አጠፋቸው፥ ሠራዊቶቻቸውንም ያጠፋቸው ዘንድ በጸሎቱ ፀሐይን በገባዖን እንደ አቆመ፥ የኤዌዎንንና የከናኔዎንን፥ የፌርዜዎንንና የኬጤዎንን፥ የኢያቡሴዎንንም ሠራዊት እስኪያጠፋቸው ድረስ ፀሐይ በሰማይ መካከል ቆሟልና በአንድ ጊዜ ሃያ ሺህ ያህል ሰውም እንደ ገደለ፥ እነርሱንም እንደ ገደላቸው፥ እግር ከአንገትም አድርጎ እንደ አሰራቸው፥ በዋሻም በጦር እንደ ገደላቸው፥ ደንጊያም እንደ ገጠመባቸው፥