ለጣዖትም ይሰግድ ነበር፤ ሙቶ ያደረውንና ደሙን፥ አባላ የተመታውንና ለጣዖቶች የተሠዋውን ይበላ ነበር፤ በሥራውም ሁሉ ያለ ፍርድ ፍጹም ቍጣና ክርክር ነበር እንጂ ፍርድ አልነበረውም። ከሥልጣኑ በታች ላሉ አሕዛብም የሚያስደነግጥ ሆኗልና እንደ ወደደ ግብርን ያስገብራቸው ነበር።