እነዚያ የመቃቢስ ልጆች ግን በሥርዐታቸው ሁሉ ይጠበቁ ነበር፤ ሞቶ ያደረውንና አባላ የተመታውን አይበሉም ነበር፤ የከለዳውያንንም ልጆች ርኵሰትና ኀጢአታቸውን ሁሉ አይሠሩም ነበር። በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ የኃጥኣንና የወንጀለኞች፥ የመናፍቃንና የከዳተኞች፥ ፍጹም ርኩሰትንና ቅሚያን የተሞሉ የአረማውያን ልጆች የሚሠሩት ሥራቸው ክፉና ብዙ ነበርና።