የተደፋፈሩ የቆሬን ልጆች ግን በምድር በታች አሰጠማቸው፤ በሥጋና በነፍስ ሕያዋን ሳሉ ከከብቶቻቸውና ከድንኳኖቻቸው ጋራ ወደ ሲኦል አወረዳቸው፤ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ወድዶታልና ከትእዛዙም አልወጣምና የተናገረው ቃል ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይደረግለት ነበር።