በምስክሩ ድንኳን ውስጥም ይቅር በሚልበት በመክደኛው ላይ ሆኖ ይናገር ነበር፤ ለመረጣቸው ለያዕቆብ ልጆች፥ በእግዚአብሔር በሕጉና በትእዛዙ ጸንተው ለሚኖሩ ለቅዱሳኑም የእግዚአብሔር ብርሃኑ ይገለጥላቸው ነበር።