ያጥኑም ዘንድ ጥናቸውን ያዙ፤ ሄደውም አጠኑ፤ እግዚአብሔር ግን ጸሎታቸውን አልተቀበለም፤ በጥናቸው እሳትም ተቃጠሉ፤ በእሳት እንደሚቀልጥ ሰምም ቀለጡ፤ ከእነርሱም አንድ ሰው ስንኳ አልቀረም፤ “በሰውነታቸው መቃጠል ጥናቸው ከብሯል” ብሏልና በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ ከገቡት ከጥናቸው በቀር ልብሶቻቸውና አጥንቶቻቸው አልቀሩም።