የእግዚአብሔርን ሰው ሙሴን አስበው፤ በጸሎቱና በትሕትናው ይህን ያህል ሕዝቡን ሲጠብቅ አልተበሳጨም፥ አላጠፋምም፤ ነገር ግን ላሙትና እግዚአብሔርም በአንድ ጊዜ ያጠፋቸው ዘንድ ለወደደ ለወንድሙና ለእኅቱ በየዋህነቱ በእግዚአብሔር ዘንድ ኀጢአታቸውን እንዲህ ሲል አስተሰረየላቸው፥ “አቤቱ ወገኖችህ በፊትህ በድለዋልና ወገኖችህን ይቅር በል፤ ቸልም አትበል፥