ኤልያስም፥ “ልጅሽን ስጪኝ” አላት፥ ከብብቷም ወስዶ ተቀምጦበት ወደ ነበረው ሰገነት አወጣው፤ በአልጋውም ላይ አስተኛው።
2 ነገሥት 4:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አውጥታም በእግዚአብሔር ሰው አልጋ ላይ አጋደመችው፤ በሩንም ዘግታበት ወጣች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ላይ ወጥታም በእግዚአብሔር ሰው ዐልጋ ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታበት ወጣች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱንም አውጥታ ለኤልሳዕ በተሠራው ክፍል በማስገባት በአልጋው ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታበት ተመልሳ ሄደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱንም አውጥታ ለኤልሳዕ በተሠራው ክፍል በማስገባት በአልጋው ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታበት ተመልሳ ሄደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወጥታም በእግዚአብሔር ሰው አልጋ ላይ አጋደመችው፤ በሩንም ዘግታበት ወጣች። |
ኤልያስም፥ “ልጅሽን ስጪኝ” አላት፥ ከብብቷም ወስዶ ተቀምጦበት ወደ ነበረው ሰገነት አወጣው፤ በአልጋውም ላይ አስተኛው።
ትንሽ ቤት በሰገነቱ ላይ እንሥራ፤ በዚያም አልጋና ጠረጴዛ፥ ወንበርና መቅረዝ እናኑርለት፤ ወደ እኛም ሲመጣ ወደዚያ ይግባ” አለችው።
መጥታም ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው፤ እርሱም፥ “ሄደሽ ዘይቱን ሽጭ ዕዳሽንም ክፈዪ፤ በተረፈውም ዘይት የአንቺንና የልጆችሽን ሰውነት አድኚ” አላት።