የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 25:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡ​ንም ይዘው የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​በት የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ዴብ​ላታ ወሰ​ዱት፤ ፍር​ድም ፈረ​ዱ​በት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሡን ያዙት። በዚያ ጊዜ ሪብላ ወደ ነበረው ወደ ባቢሎንም ንጉሥ አመጡት፤ በዚያም የባቢሎን ንጉሥ ፈረደበት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሴዴቅያስም ተይዞ በሪብላ ከተማ ወደሚገኘው ወደ ናቡከደነፆር ተወሰደ፤ በዚያም ናቡከደነፆር ፍርድ አስተላለፈበት፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሴዴቅያስም ተይዞ በሪብላ ከተማ ወደሚገኘው ወደ ናቡከደነፆር ተወሰደ፤ በዚያም ናቡከደነፆር ፍርድ አስተላለፈበት፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡንም ይዘው የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ሪብላ አመጡት፤ ፍርድም ፈረዱበት።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 25:6
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ ፈር​ዖን ኒካዑ በኤ​ማት ምድር ባለ​ችው በዴ​ብ​ላታ አሰ​ረው፤ በም​ድ​ሩም ላይ መቶ መክ​ሊት ብርና አንድ መቶ መክ​ሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለ​በት።


የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ንጉ​ሡን ተከ​ተሉ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በኩል ባለው ሜዳ ያዙት፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ከእ​ርሱ ተለ​ይ​ተው ተበ​ት​ነው ነበር።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ሠራ​ዊት አለ​ቆች አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ ምና​ሴ​ንም በዛ​ን​ጅር ያዙት፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዱት።


ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርና ከሰ​ይፍ፥ ከራ​ብም በዚ​ህች ከተማ የቀ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ሹት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ስለት ይመ​ታ​ቸ​ዋል፤ አያ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ም​ራ​ቸ​ውም።”


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ በእ​ው​ነት በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰ​ጣል፤ አፍ ለአ​ፍም ይና​ገ​ረ​ዋል፤ ዐይን ለዐ​ይ​ንም ይተ​ያ​ያሉ እንጂ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ አያ​መ​ል​ጥም፤


አን​ተም በር​ግጥ ትያ​ዛ​ለህ፤ በእ​ጁም አል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለህ እንጂ ከእጁ አታ​መ​ል​ጥም፤ ዐይ​ን​ህም የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ዐይን ታያ​ለች፤ እር​ሱም ከአ​ንተ ጋር አፍ ለአፍ ይና​ገ​ራል፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ትገ​ባ​ለህ።


ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንና ልጆ​ች​ህ​ንም ሁሉ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን ያወ​ጣሉ፤ አን​ተም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትያ​ዛ​ለህ እንጂ ከእ​ጃ​ቸው አታ​መ​ል​ጥም፤ ይህ​ችም ከተማ በእ​ሳት ትቃ​ጠ​ላ​ለች።”


ንጉ​ሡ​ንም ይዘው የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​ባት በኤ​ማት ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ዴብ​ላታ አመ​ጡት፤ እር​ሱም ፍር​ድን በእ​ርሱ ላይ ተና​ገረ።