የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 25:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ንጉ​ሡን ተከ​ተሉ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በኩል ባለው ሜዳ ያዙት፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ከእ​ርሱ ተለ​ይ​ተው ተበ​ት​ነው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሁን እንጂ የባቢሎናውያንም ሰራዊት ንጉሡን ተከታትሎ በማሳደድ በኢያሪኮ ሜዳ ላይ ደረሱበት። ወታደሮቹም ሁሉ ተለይተውት ተበታትነው ሳለ

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የባቢሎን ሠራዊት ግን ንጉሥ ሴዴቅያስን እያሳደደ በኢያሪኮ አጠገብ በሚገኝ ሜዳ ላይ ማረከው፤ ወታደሮቹም ጥለውት ሸሹ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የባቢሎን ሠራዊት ግን ንጉሥ ሴዴቅያስን እያሳደደ በኢያሪኮ አጠገብ በሚገኝ ሜዳ ላይ ማረከው፤ ወታደሮቹም ጥለውት ሸሹ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የከለዳውያንም ሠራዊት ንጉሡን ተከታተሉ፤ በኢያሪኮም ሜዳ ያዙት፤ ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ተለይተው ተበትነው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 25:5
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተሰ​በ​ረች፤ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ሁሉ በሁ​ለት ቅጥር መካ​ከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አት​ክ​ልት በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በሌ​ሊት ሸሹ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደ​ውም መን​ገድ ሄዱ።


ንጉ​ሡ​ንም ይዘው የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​በት የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ዴብ​ላታ ወሰ​ዱት፤ ፍር​ድም ፈረ​ዱ​በት።


ነገር ግን፥ በፈ​ረስ ላይ ተቀ​ም​ጠን እን​ሸ​ሻ​ለን እንጂ እን​ዲህ አይ​ሆ​ንም አላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ፤ ደግ​ሞም በፈ​ጣን ፈረስ ላይ እን​ቀ​መ​ጣ​ለን አላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ችሁ ፈጣ​ኖች ይሆ​ናሉ።


ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርና ከሰ​ይፍ፥ ከራ​ብም በዚ​ህች ከተማ የቀ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ሹት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ስለት ይመ​ታ​ቸ​ዋል፤ አያ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ም​ራ​ቸ​ውም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፥ “ከክ​ፋቱ የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል እንደ ክፉው በለስ፥ እን​ዲሁ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፤ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ በዚች ሀገር የሚ​ቀ​ሩ​ት​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅሬታ፥ በግ​ብ​ጽም ሀገር የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን እን​ዲሁ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አን​ተም በር​ግጥ ትያ​ዛ​ለህ፤ በእ​ጁም አል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለህ እንጂ ከእጁ አታ​መ​ል​ጥም፤ ዐይ​ን​ህም የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ዐይን ታያ​ለች፤ እር​ሱም ከአ​ንተ ጋር አፍ ለአፍ ይና​ገ​ራል፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ትገ​ባ​ለህ።


የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ተከ​ታ​ተ​ላ​ቸው፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም በኢ​ያ​ሪኮ ሜዳ አገ​ኙት፤ ይዘ​ውም በሐ​ማት ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ዴብ​ላታ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር አመ​ጡት፤ እር​ሱም ፍር​ድን በእ​ርሱ ላይ ተና​ገረ።


የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ንጉ​ሡን ተከ​ታ​ተ​ሉት፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ሜዳ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን ያዙ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ ተበ​ት​ነው ነበር።


ጋሜል። ይሁዳ ስለ ውር​ደ​ቷና ስለ ባር​ነቷ ብዛት ተሰ​ደ​ደች፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ተቀ​መ​ጠች፤ ዕረ​ፍ​ትም አላ​ገ​ኘ​ችም፤ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አት መካ​ከል ያዙ​ዋት።


ዋው። ከጽ​ዮን ሴት ልጅ ውበት ሁሉ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ አለ​ቆ​ችዋ መሰ​ማ​ሪያ እን​ደ​ማ​ያ​ገኙ አውራ በጎች ሆኑ፤ ከሚ​ያ​ባ​ር​ሩ​አ​ቸው ፊት ተዳ​ክ​መው ሄዱ።


የሚ​ረ​ዱ​ት​ንም፥ በዙ​ሪ​ያው ያሉ​ትን ሁሉ፥ ጭፍ​ሮ​ቹ​ንም ሁሉ ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ሰይ​ፍን እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


ያመ​ለ​ጡ​ትም ሁሉ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የቀ​ሩ​ትም ሁሉ ወደ እየ​ነ​ፋ​ሳቱ ይበ​ተ​ናሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ርሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


“አን​ተም ለእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ይህን ሙሾ አሙ​ሽ​ለት፤