እስከ ሁለትና እስከ ሦስት ቀን ድረስ ያልተገኙና ያልደረሱ ሁሉ እንደ ሥርዐታቸው በአለቆቻቸው ቅጣት ይቀጡ ዘንድ፥ ከብቶቻቸውም ይወረሱ ዘንድ፥ እነርሱም ከወገኖቻቸው ይለዩ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ዐዋጅ ነገረላቸው።