እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ሌላዎች የይሁዳ ክፍሎች ተመለሱ። ሁሉንም በየከተሞቻቸው ላካቸው፤ እነዚህም አስቀድመው ከተሾሙላቸው ከመጀመሪያዎቹ ሹሞች፥ ከኢያሱና ከዘሩባቤል፥ ከነህምያ፥ ከዛርያስ፥ ከሬስያስ፥ ከኤኔንዮስ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከቦኤልሰሮስ፥ ከአስፈራሶስ፥ ከሬልዮስ፥ ከኢሮምዮስና ከበዓናስ ጋር የመጡ ናቸው።