ከዚህ በኋላ ራቲሞስና ጸሓፊው ስልምዮስ፥ ከእነዚህም በታች ያሉት ንጉሡ አርጤክስስ የጻፋትን ያችን መልእክት ባነበቧት ጊዜ ከብዙ ሰዎች ጋር በብዙ ችኮላ ወደ ኢየሩሳሌም ፈረሶቻቸውን አስነሡ፤ የሚሠሩትንም ይከለክሉ ጀመሩ።