የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ቆሮንቶስ 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መጀ​መ​ሪያ በጻ​ፍ​ሁት መል​እ​ክት ባሳ​ዝ​ና​ች​ሁም እንኳ አያ​ጸ​ጽ​ተ​ኝም፤ ብጸ​ጸ​ትም፥ እነሆ ያች መል​እ​ክት ለጥ​ቂት ጊዜ ብቻ እን​ዳ​ሳ​ዘ​ነ​ቻ​ችሁ አያ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በመልእክቴ ባሳዝናችሁም በዚህ አልጸጸትም፤ ብጸጸትም እንኳ መልእክቴ ያሳዘናችሁ ለጥቂት ጊዜ እንደ ሆነ ተረድቻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመልእክቴ ያሳዘንኋችሁ ብሆን እንኳ አልጸጸትም፤ የተጸጸትሁ ብሆን እንኳ፥ ያ መልእክት ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘናችሁ ተረድቻለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በፊት የጻፍኩላችሁ መልእክት ያሳዘናችሁ ቢሆንም እንኳ መልእክቱን በመጻፌ አልጸጸትም፤ ተጸጽቼም ብሆን እንኳ የተጸጸትኩት መልእክቴ ለጥቂት ጊዜ ስላሳዘናችሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመልእክቴ ያሳዘንኋችሁ ብሆን እንኳ አልጸጸትም፤ የተጸጸትሁ ብሆን እንኳ፥ ያ መልእክት ጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘናችሁ አያለሁና አሁን ለንስሐ ስላዘናችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ስላዘናችሁ አይደለም፤

ምዕራፉን ተመልከት



2 ቆሮንቶስ 7:8
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያሳ​ዘ​ነ​ውን ሰው እንደ ይቅ​ር​ታው ብዛት ይም​ረ​ዋ​ልና፤


ነገር ግን ይህን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ በል​ባ​ችሁ ኀዘን ሞላ።


ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።


እነሆ፥ ያ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብላ​ችሁ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ኀዘን ምንም የማ​ታ​ውቁ እስከ መሆን ደር​ሳ​ችሁ፥ ራሳ​ች​ሁን በበጎ ሥራና በን​ጽ​ሕና እስ​ክ​ታ​ጸኑ ድረስ፥ ትጋ​ት​ንና ክር​ክ​ርን፥ ቍጣ​ንና ፍር​ሀ​ትን፥ ናፍ​ቆ​ት​ንና ቅን​ዐ​ትን፥ በቀ​ል​ንም አደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ፤


ይህን የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እኛ እንደ ተጋ​ችሁ ይታ​ወቅ ዘንድ ነው እንጂ ስለ በደ​ለና ስለ ተበ​ደለ ሰው አይ​ደ​ለም።


ነገር ግን ያዘ​ኑ​ትን የሚ​ያ​ጽ​ናና እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቲቶ መም​ጣት አጽ​ና​ናን።


በመ​ም​ጣቱ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በአ​ጽ​ና​ና​ች​ሁት ማጽ​ና​ና​ትም ነው እንጂ፤ ለእኛ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ቡና እን​ደ​ም​ት​ቀኑ ፍቅ​ራ​ች​ሁን ነግ​ሮ​ናል፤ ይህ​ንም ሰምቼ ደስ​ታዬ በእ​ና​ንተ በዛ።


አሁን ግን እኔ ስለ እርሷ በብዙ ደስ ይለ​ኛል፤ ደስ​ታ​ዬም ስለ አዘ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ንስሓ ልት​ገቡ ስለ አዘ​ና​ችሁ እንጂ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ ስንኳ እን​ዳ​ይ​ጠፋ፥ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብላ​ችሁ አዝ​ና​ች​ኋ​ልና።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።